Psalms 128

የጻድቃን በረከት

መዝሙረ መዓርግ።

1 እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ፣
በመንገዱም የሚሄዱ የተባረኩ ናቸው።
2የድካምህን ፍሬ ትበላለህ፤
ትባረካለህ፤ ይሳካልሃልም።
3ሚስትህ በቤትህ፣
እንደሚያፈራ ወይን ናት፤
ወንዶች ልጆችህ በማእድህ ዙሪያ፣
እንደ ወይራ ተክል ናቸው።
4እነሆ፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው፣
እንዲህ ይባረካል።

5 እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ፤
በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ያሳይህ፤
6የልጅ ልጅ ለማየትም ያብቃህ።

በእስራኤል ላይ ሰላም ይውረድ።
Copyright information for AmhNASV